Loading...
アイコン

Yishak Sedik Official

チャンネル登録者数 11.9万人

9万回視聴 ・ 1955いいね ・ 2022/08/21

   • ነፍሴ ተጠማች//Nefse Tetemach//ይስሐቅ ሰድቅ//yishak...…

አሁንም አሁንም( ነፍሴ ተጠማች/2*/)
ለማየት ክብርህን      "     "
ዛሬም መገለጥክን     "     "
ለመጥገብ ሞገስህን  "     "
           የአምላኬንስ ፊት መች አየዋለሁ
            ወደ ክብሩስ ሙላት መች እደርሳለሁ
ስትል ድምፅ አሰማች (ነፍሴ ተጠማች/2*/)
          አላፊው ጠፊው ልቤን ላይማርከው
          ኢየሱስ አንተን ሳይ ነው የምጠግበው
ስትል ድምፅ አሰማች (ነፍሴ ተጠማች/2*/)

ወደ ውሀ ምንጭ ዋላ ተጠምታ
እንደምትናፍቅ ልትረካ ሽታ
እንዲሁ ናፍቃለች አንተን ብቻ ጌታ
ነፍሴ ወዳሀለች ገና ድምፅህን ሰምታ
እንዲሁ ናፍቃለች እንድታይህ ጌታ
ነፍሴ ወዳሀለች ገና ቃልህን ሰምታ
             አንተ ብቻ ታይ/3*/
            በመቅደስህ ላይ
            አንተ ብቻ ታይ/3*/
            በህይወቴ ላይ

የነፍሴ መሻት ርሀብ እና ጥማት
ክብርህን ማየት ነው ዘወትር ሳደምጣት
ፍለቅ የህይወት ውሀ ኢየሱስ ብሩክ ምንጭ
ምንም አያግኛት ነፍሴን ከክብርህ ውጪ
          አንተ ጌታዬ ነህ ጌታዬ አንተ ጌታዬ ነህ
          አንተ ንጉሴ ነህ ንጉሴ አንተ ንጉሴ ነህ
ልቤ ወደደህ አከበረህ
ዛሬም ለነፍሴ ውዷ አንተ ነህ /4*/


በእምነት ትዘልቃለች ወደ ክብርህ ጓዳ
ሀይልህን ማዳንክን ልታይ ነፍሴ ወዳ
አይኖቼም ናፈቁህ መቅደስህ ገብቼ
ነፍሴ ክብርህን ትይ ልርካ አንተን አጊኝቼ

          አንተ ጌታዬ ነህ ጌታዬ አንተ ጌታዬ ነህ
          አንተ ንጉሴ ነህ ንጉሴ አንተ ንጉሴ ነህ
ልቤ ወደደህ አከበረህ
ዛሬም ለነፍሴ ውዷ አንተ ነህ  /*4/

コメント

コメントを取得中...

コントロール
設定

使用したサーバー: directk